Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ሃገራት ወደ ብሪታኒያ የሚደረግ ጉዞን ሲያግዱ ሳዑዲ ደግሞ ዓለም አቀፍ በረራዎችን አቁማለች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በደቡብ ምስራቅ እንግሊዝ እየተስፋፋ በሚገኘው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተለያዩ የዓለም ሃገራት ወደ ብሪታንያ የሚደረጉ በረራዎችን ማቆማቸውን አስታወቁ፡፡

በትናንትናው ዕለት የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በአዲሱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ከገና ጋር በተያያዘ የሚደረጉ ግብይቶች መሰረዛቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ጀርመን፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ አርጀንቲና፣ ቺሊ፣ ኮሎምቢያ እና ሌሎች ሃገራት ወደ ብሪታንያ የሚደረግ በረራን አግደዋል፡፡

በተመሳሳይ ሳዑዲ ዓረቢያ በአዲሱ የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ዓለም አቀፍ በረራዎች ማቆሟን ገልጻለች፡፡

ሳዑዲ ለአንድ ሳምንት ባቆመችው ጉዞ በየብስ እና በባህር የሚጓዙትን እንደሚጨምርም ነው የገለጸችው፡፡

ደቡብ ኮሪያ አምስት እና ከዚያ በላይ በመሆን በቡድን መሰብሰብን ማገዷን አስታውቃለች፡፡

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ በመስከረም ወር በብሪታንያ መከሰቱን የዓለም ጤና ድርጅት የገለጸ ሲሆን መጀመሪያ ከተከሰው ቫይረስ ይልቅ የመሰራጨት ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ነው የጠቀሰው፡፡

እስካሁን በዓለም ላይ 76 ነጥብ 7 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 1 ነጥብ 69 ሚሊየን ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

 

ምንጭ፡-አልጀዚራ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.