Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት ለመከላከያ ሰራዊት እና ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳንጉር ወረዳ፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የጥሩነሸ ቤጂንግ ሆስፒታል ለመከላከያ ሰራዊት እና ተፈናቃዮች ድጋፍ አድርገዋል፡፡
 
በመተከል ዞን የዳንጉር ወረዳ ነዋሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞች የህግ የበላይነትን እያስከበረ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማበርከታቸውን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ድጋፉ የጸጥታ ሃይሎች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር እያደረጉት ያለውን መስዋዕትነት በመረዳት እና የተጀመረው ዘላቂ ሰላምን የማስፈን ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማስቻል የተደረገ መሆኑን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ክንፉ ገልጸዋል።
 
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራሮች፣ የመሰረታዊ ሠራተኞች ማህበር እና ሠራተኞች በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት የአልባሳት እና የዕለት ደራሽ የምግብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
 
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ስር የሚገኘው የጥሩነሸ ቤጂንግ ሆስፒታልም ከ3 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የህክምና ግብዓቶችን አፋር ክልል ለሚገኘው ጃራ ጤና ጣቢያ አስረክቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.