Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት በግንባር በመገኘት ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትና የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን ለመከላከያ ሠራዊት ከ28 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለመከላከያ ሰራዊት ከ18 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ ነው ያደረገው፡፡

ድጋፉን ግንባር በመገኘት ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ሰብሳቢ ሙሉጌታ አበበ፥ ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን መሆናችንን ለማሳየት እዚህ ተገኝተናል ብለዋል፡፡

ከዚህ በኋላም ሰራዊቱ ለሚያደርገው ኢትዮጵያን የማዳን ተግባር ሁሉ ከጎናችሁ ነን ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላለፉት ዓመታት ሰብዓዊም ቁሳዊም ኪሳራ ደርሶባቸዋል ያሉ ሲሆን፥ አሁን ደግሞ ኢትዮጵያውያን አንድ ላይ በመሆን የሽብር ቡድኑ እስኪደመሰስ ድረስ በጋራ መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ፥ የሽብር ቡድኑን በመደምሰስ ሂደት ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን ነን፤ ይህን የሽብር ቡድን ለማጥፋትም ሁላችንም ልንረባረብ ይገባል ነው ያሉት፡፡

በተመሳሳይ የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን ግንባር በመገኘት ያስረከቡት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳንዶካን ደበበ በበኩላቸው፥ ኮርፖሬሽኑ ለመከላከያ ሰራዊቱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት ኮለኔል ሙስጠፋ የሱፍ “ዘመቻ ለኀብረ ብሔራዊ አንድነት”ከተጀመረ ጀምሮ ለሰራዊቱ ያደረጋችሁትን ድጋፍ አንረሳም ያሉ ሲሆን፥ ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በብስራት መንግስቱ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.