Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ አመራሮች ሲያካሂዱት የነበረውን ውይይት አጠናቀቁ

የተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ አመራሮች ሲያካሂዱት የነበረውን ውይይት አጠናቀቁ
 
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሲያካሂዱት የነበረውን ውይይት አጠናቀዋል፡፡
 
የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄዱት የነበረው የምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል፡፡
 
የምክክር መድረኩ ዓላማ ከድል በኋላ የተፈጠሩ መዛነፎችን ለማረም እና በክልሉ ያለውን አመራር ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ ማድረግን ያለመ እንደነበር ተገልጿል፡፡
 
የሽብር ቡድኑ ወረራ ከፈጠረው ዘርፈ ብዙ ችግሮች በፍጥነት ለመውጣት አመራሩ ቁርጠኛ እና የጋራ ግንዛቤ እንዲይዝ መደረጉን የክልሉ ኮሙኒኬሽ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ተናግረዋል፡፡
 
የአፋር ክልል መንግስት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮችም በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ እና በድህረ ጦርነት መዛነፎች እና እርምቶች በሚል መሪ ቃል ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩት የውይይት መድረክ ዛሬ ተጠናቋል፡፡
 
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አዋል አርባ፥ ኢትዮጵያን የማፍረስ አጀንዳ ያላቸውን የውስጥና የውጭ ኃይሎችን ወረራ እየመከትን የተጀመሩ የብልጽግና ጉዞ ማስቀጠል የሚያስችሉ ዘላቂ ሠላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በትኩረት እንደሚሠራም ገልጸዋል።
 
በተመሳሳይ የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሲያካሂዱት የነበረው ውይይት ዛሬ ተጠናቋል፡፡
 
በውይይቱ ማጠናቀቂያ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እንደገለጹት፥ ተገደን በገባንበት ጦርነት የላቀ ድል ከማስመዝገብ ባለፈ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በማረጋገጥ ፈጥነን ወደ ልማታችን መመለስ አብይ ትኩረታችን ሊሆን ይገባል ።
 
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳዳር ከፍተኛ አመራሮችንም ለአራት ተከታታይ ቀናት በድህረ ጦርነት ስትራቴጂ ዙሪያ ሲያካሂዱት የቆዩትን የምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት አጠናቀዋል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.