Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን አስመረቁ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ቀብሪ ደሀር ፣ ወለጋ እና አርሲ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻቸውን አስመረቁ፡፡

ጅማ ዩኒቨርስቲ እና ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል፡፡

ጅማ ዩኒቨርስቲ በሁለተኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 4ሺህ 311 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 3ሺህ 950 በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 1ሺህ 530 ሴቶች ናቸው።

በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ 45 ሴቶች የሚገኙበት 354 ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡

በተጨማሪም ሶሰት ተማሪዎች በሶስተኛ ዲግሪ እና አራት ተማሪዎች ደግሞ የ “ሰብ ስፔሻሊቲ” ተመራቂ ይገኙበታል፡፡

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ጥቅምት ወር 1ሺህ 409 ተማሪዎችን ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

ወለጋ ዩኒቨርሲቲም በተመሳሳይ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 398 ተማሪዎችን ዛሬ በወለጋ ስታዲየም አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል የመጀመሪያ ዲግሪ 3 ሺህ 13፣ በሁለተኛ ዲግሪ 344፣ በህክምና ዶክትሪት 40 እና የአካዳሚክ ዶክተር በአጠቃላይ 3 ሺህ 398 ናቸው።

ቀብሪ ደሀር ዩኒቨርሲቲም የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎች የክልልል እና የፌዴራል የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎቹን አስመርቋል፡፡

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ በህክምና ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 23 ሰልጣኞቹን በመጀመሪያ ዙር አስመርቋል፡፡

በተመሳሳይም የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸው 2 ሺህ 39 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች የአስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በተያያዘም የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 576ተማሪዎች ሲያስመርቅ፥ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ሁርካቶ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የአማራ አመራር አካዳሚ ለመጀመሪያ ጊዜ 37 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን፥ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር አካዳሚው ለዚህ የበቃው በሠራተኞች ድካም በርካታ ፈተናዎችን አልፎ ነው ብለዋል፡፡

ወቅቱ በአንድ በኩል ትልልቅ እና አስደሳች ውጤቶች የተመዘገቡበት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ፈተናዎች የበዙበት ሀገራዊና ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሀገሪቱ በቀጣይ የምትፈልገውን ከችግር መውጫ መንገድ መቀየስ ወሳኝ መሆኑንም ነዚህ ወቅት ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ኢትዮጵያዊነት የማይደበዝዝ ይልቁንም በይበልጥ የሚደምቅና የሚፈካ የጋራ ማንነታችን ሊሆን ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.