Fana: At a Speed of Life!

የተመዘገበውን አገራዊ ድል አስጠብቆ መዝለቅ ይገባል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በድህረ ጦርነት ድላችንን አስጠብቆ መዝለቅ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ መለሰ አለሙ የተገኘውን አገራዊ ድል ዘላቂ በማድረግ ብልፅግናን እውን ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች ÷ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግንባር ድረስ በመዝመት ለአገርና ለህዝብ መኖርን በተግባር ስላሳዩን አርአያቸውን ተከትለን ሁሌም ከጎናቸው እንቆማለን ብለዋል፡፡

በውይይቱ ከንቲባ አዳነች÷አሸባሪው ህወሃት ኢትዮጵያን ለማፍረስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ጦርነት መክፈቱን በማስታወስ በሞራልና በስንቅ ብቻም ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያውያን በጋራ በመዝመት የጋራ ድል መጎናፀፉን አስረድተዋል።

በአንድነት ከቆሙ የማያሸንፉት ሀይል አለመኖሩን በአድዋ ታሪክ የሚያወሱት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ዛሬም እያስመሰከሩት ያለ ሀቅ መሆኑንም ነው ከንቲባ አዳነች ያስገነዘቡት።

በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖችንና የዘማች ቤተሰቦችን በማቋቋም እንዲሁም የወደሙ ንብረቶችን በጋራ በመገንባት በድህረ ጦርነት ድላችንን አስጠብቆ መዝለቅ እንደሚገባ ከንቲባዋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያን ለማዳን ሁሉም መክፈል ያለበትን መስዋዕትነት ለመክፈል በመቁረጡ ጦርነት የሚያስከትለውን ዘርፈ ብዙ ተፅዕኖ ተቋቁመን ለሌላ ድል በጋራ ቁመናል ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ÷ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዲሞክራሲያዊ ባህል ግንባታና ህዝባዊ አንድነትን በመገንባት ለኢትዮጵያ ካበረከቱት የላቀ ተግባር በተጨማሪ፥ ግንባር ድረስ በመዝመት ለአገርና ለህዝብ መኖርን በተግባር አሳይተውናልና አርአያቸውን ተከትለን ሁሌም ከጎናቸው እንቆማለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.