Fana: At a Speed of Life!

የተመድ ዋና ፀሐፊ በኮሮና ክትባት አጠቃቀም ዙሪያ የሚታየውን  ኢ – ፍትሐዊ አካሄድ ኮነኑ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ 10 የዓለም ሃገራት 75 በመቶ የሚሆነውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት መጠቀማቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህ አካሄድም ፍትሐዊነት አይታይበትም ሲሉ ነው ዋና ጸሐፊው የኮነኑት፡፡

ጉተሬዝ በሁሉም ሃገራት ለሚገኙ ዜጎች ክትባቱ እንዲዳረስ የበለጸጉ ሃገራትን ተማጽነዋል፡፡

ዋና ጸሐፊው ተማጽኗቸውን ያቀረቡት በትናንትናው ዕለት የጸጥታው ምክር ቤት በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

እስካሁንም 130 ሀገራት አንዲትም መጠን ክትባት አለማግኘታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

ጉተሬዝ በዚህ ፈታኝ ወቅት የኮሮና ቫይረስ ፍትሐዊ ተደራሽነት የሞራል ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ብለዋል፡፡

የተከሰተውን ችግር ለመቅረፍም የቡድን 20 ሃገራት የአስቸኳይ ጊዜ ግብረ-ኃይል እንዲያቋቁሙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ የሚገኙ 32 ሃገራት ከ100 በታች የሚሆነውን ክትባት ማዘዛቸው ነው የተነገረው፡፡

 

ምንጭ፡-አልጀዚራወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.