Fana: At a Speed of Life!

የተመድ የሰብአዊ መብቶች ረዳት ዋና ጸሐፊ ከነገ ጀምሮ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ረዳት ዋና ጸሐፊ ኢልዜ ብራንድስ ኬሪስ ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ።

ጉብኝታቸው ለሶስት ቀናት እንደሚቆይ የተመድ ሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮ አስታውቋል።

ረዳት ዋና ጸሐፊዋ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣የአፍሪካ ሕብረትና የአውሮፓ ሕብረት በጋራ ያዘጋጁት “አፍሪካን ዩኒየን ኮምፕሊያንስ ኤንድ አካውንተብሊቲ ፍሬምወርክ” የተሰኘ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ገልጸዋል።

ጸሐፊዋ ከግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ቀናት በደቡብ ሱዳን ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

ኢልዜ ብራንድስ ኬሪስ ከፈረንጆቹ ጥር 2020 ጀምሮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ረዳት ዋና ጸሐፊ ሆነው በመስራት ላይ ይገኛሉ።

ኢልዜ የተመድ ሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ የኒው ዮርክ ቅርንጫፍ ኃላፊ መሆናቸውን ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.