Fana: At a Speed of Life!

የተመድ የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ ካትሪን ሱዚ እና የ5 አገራት አምባሳደሮች ጅግጅጋ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ ዶክተር ካትሪን ሱዚ ፣ የጣሊያን፣ ጃፓን ፣ ስዊዘርላንድ ፣ ቼክሪፐብሊክ እና ፊንላንድ አምባሳደሮች እና የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት፣ ዩኒሴፍ ፤ ፋኦና አይ ኦ ኤም ኃላፊዎች ረፋዱን ጅግጅጋ ገብተዋል።

የልዑካን ቡድኑ ገራድ ዊል ዋል ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ሀላፊ ዶክተር ሁሴን ሀሺ ቃሲም፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አያን አብዲና ሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሀላፊዎቹ በጅግጅጋ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ በክልሉ ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን መልሶ ማቋቋም በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.