Fana: At a Speed of Life!

የተበላሸና የጠፋ የተሽከርካሪ ሰሌዳን ለመቀየር እየገጠመን ባለው እንግልት ተማረናል-የተሽከርካሪ ባለንብረቶች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተበላሸና የጠፋ የተሽከርካሪ ሰሌዳን ለመቀየር እየገጠመን ያለው እንግልት አማሮናል ሲሉ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ቅሬታ አቀረቡ።
 
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በአገልግሎት መስጫ አካባቢዎች ቅኝት ባደረገበት ወቅት ተገልጋዮች አገልግሎቱን ለማግኝት ከዚህ ቀደም በአንድ ቀን እንደሚያልቅና አሁን ላይ ግን ከ5 እስከ 10 ቀናት በላይ በመውሰዱ ለአላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት መዳረጋቸውን ተናግረዋል።
 
በተለያዩ ምክንያቶች ተበለሽተው ለመታየት አስቸጋሪ የሆኑ እና የጠፉ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎችን የመቀየር ስራ ከአሁን በፊት የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የነበረ ሲሆን፥ አሁን ላይ ግን በአዲስ አደረጃጀት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ አገልግሎት ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት ስራውን ተረክቦ እየሰራ ይገኛል።
 
በፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን አንባቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በርክክብ ወቅት ለተወሰኑ ቀናት አገልግሎቱን ለተገልጋዩ ህብረተሰብ በወቅቱ ማድረስ እንዳልተቻለ ጠቅሰው÷አሁን ላይ ግን በሙሉ አቅሙ እና የእረፍት ቀናትን በመጨመር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
 
ከዚህ ቀደም አዲስ የተሽከርካሪ ሰሌዳን ጨምሮ አገልግሎት የሚሰጡት በቀን እስከ 300 ብቻ እንደነበርና አሁን ላይ ግን ይህን ቁጥር ከፍ በማድርግ የተገልጋዩን ፍላጎት ለማሳካት በቀን አዲስ ሰሌዳን ጨምሮ ከ3 ሺህ በላይ አየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል።
 
በቀጣይ በዘመናዊ አሰራር የተገልጋዩን ቅሬታ ለመፍታት እንደሚሰሩም ነው የተናገሩት።
 
ህዝብን በተሰማሩበት የስራ መስክ በቅንነት እና በታማኝነት ማገልገል አሁን ሀገራችን ካለችበት ሁኔታ አንጻር አስፈላጊ እና ግዴታ በመሆኑ ፐብሊክ ስርቪስ ትራንስፖርት ተቋምም ይህን በቁርጠኝነት እና በታማኝነት ተገልጋዩን ህዝብ እያገለገሉ በተሰማሩበት ግንባር እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

በሲሳይ ጌትነት

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.