Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና የኳታር ልዑካን ከሦስት ዓመታት በኋላ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶችና የኳታር ልዑካን ከሦስት ዓመታት በኋላ በኩዌት ተገናኝተው መወያየታቸው ተሰምቷል፡፡

የባህረሰላጤው የትብብር ምክር ቤት አባል የነበረችው ኳታር በፈረንጆቹ 2017 በሃገራቱ ዘርፈ ብዙ ማዕቀብ ተጥሎባት ቆይቷል፡፡

ባለፈው ወርም የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶችን ጨምሮ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ግብጽ እና ባህሬን ከኳታር ጋር ያቋረጡትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጀምረዋል፡፡

ኳታርም ስምምነቱን ተከትሎ የአየር እና የየብስ ግንኙነቷን ከሃገራቱ ጋር ጀምራለች፡፡

ከስምምነቱ በኋላ ሁለቱ ሃገራት በይፋ ሲወያዩ የመጀመሪያቸው ነው ተብሏል፡፡

ውይይቱም በባህረሰላጤው የትብብር ምክር ቤት በተደረሰው ስምምነት እና ትግበራ ዙሪያ ለመምከር ያለመ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.