Fana: At a Speed of Life!

የተከለሰው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ወደ ስራ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተከለሰው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ወደ ስራ መግባቱ ተገለጸ፡፡

ፖሊሲው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዋና ዋና ግቦች፣ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ሀገራዊ ምርትን ማሳደግ፣ አዳዲስ ሀብት መፍጠርና አካታችን ይዞ የተከለሰ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ የተከለሰውን ፖሊሲ በሚመለከት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

የተከልሰው ፖሊሲ በቴክኖሎጅ የታገዝ ፈጣን ኢኮኖሚን ለመገንባት፣ የሰለጠነና ብቁ የሰው ኀይልን ለመፍጠር ታስቦ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ምርምርና ልማት፣ የቴክኖሎጂ ልማት ሽግግር፣ የዕውቀት አሥተዳደር፣ የኢኖቬሽን እና ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ አካባቢያዊና ባህላዊ ልማት በዋናነት ፖሊሲው ሊተግብራቸው ያሰባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

ሚያዝያ 2014 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው ይህ ፖሊሲ የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን፣ የአፍሪካ 2063 አጀንዳንና 2024 የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ስትራቴጂን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዓለም አቀፍ ደረጀ የመደራደር አቅም ያለው የሰው ሃይል እንዲገነባ፣ ልዩ ተሰጥኦና ተውህቦ ላለቸው ዜጎች እንዲሁም በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የሙያ ዘርፎች በቂና ብቁ ባለሙያዎችን ገበያና ቴክኖሎጂ ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ ማፍራት በፖሊሲው ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.