Fana: At a Speed of Life!

የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነብርሃን ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነብርሃን ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ-ክርስቲያን ተፈጸመ።

በስርዓተ  ቀብሩ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የመንግስት ተቋማት የሩሲያ ኤምባሲ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ማህበራት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነ ብርሃን በተለያዩ መስኮች ካበረከቱት አስተዋኦዖ መካከልም በአገሪቷ ሰላምና ወንድማማችነት እንዲጎለብት በእርቀ ሰላም በኩል የሰሩት ስራ አንዱ ነው።

በላየንስ ክለብ ለረጅም ዓመታት የሰጡት አገልግሎት፣ በቀይ መስቀል ማህበርና በኢትዮጵያ ስካውት ማህበር በኩል አገር ወዳድ ወጣት እንዲፈራ በማድረግ ረገድ በርካታ ስራዎችን ሰርተው ያለፉ ናቸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.