Fana: At a Speed of Life!

የተገኘው ድል እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሷል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተካሄደው ዘመቻ በጠላት እጅ የነበሩት ዋና ዋና ቦታዎች ማለትም ደሴ፣ ኮምቦልቻ እና ባቲን ጨምሮ ሌሎችም አካባቢዎች በወገን ጦር እጅ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡
በተጨማሪም ሸዋ፣ የከሚሴ ልዩ ዞን እና የአፋር ክልል ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ደቡብ ጎንደርን ጨምሮ አብዛኛው የአማራ ክልል ነጻ መውጣታቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን እስከሚደመሰስ ድረስ ዘመቻው እንደሚቀጥልም ነው የገለጹት፡፡
ለኮማንዶዎች ባስተላለፉት መልዕክትም ድሉ ይቀጥላል የሚያቆም ነገር የለም ጠላት ይመታል እናንተም ታሸንፋላችሁ ብለዋል።
የጠላትን የ4 እና 5 ወር ጉዞ በ15 ቀናት ውስጥ መጨረስ ተችሏል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ባንዲራ በሌቦች በዘራፊዎች አይደፈርም በኮማንዶዎች ይጠበቃልም ብለዋል ባደረጉት ንግግር።
ህይወታችሁ እስካለ ድረስ ይህችን ባንዲራ ጠብቋት ሲሉም ለወታደሮቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው መስዋዕትነት የከፈልነው ልንሰርቅ አይደለም ልንዘርፍ አይደለም ኢትዮጵያን ለማዳን ነው ብለዋል።
ተገደን፣ ተገፍተን ለምነን በገባንበት ጦርነት በእውር ድንብር የገባው ጠላት በእውር ድንብር እንዳይወጣ ስራ ተሰርቷል የተገኘውም ድል ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ አትሸነፍም አንገቷን ቀና አድርጋ የምትሄድ አገር ናት እኛም የለመድነው ጀግንነትን ማስቀጠል ነው ብለዋል በንግግራቸው።

ኢትዮጵያ አሸንፋለች፤ የተገኘው ድል ለማመን ይከብዳል፤ ይህንኑ በሰላም በልማት ማረጋገጥ ያስፈልጋል እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከግንባር ባስተላለፉት መልዕክት።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.