Fana: At a Speed of Life!

የተጎዱ ወገኖችን ለማገዝ ዜጎች እንዲረባረቡ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የተጎዱ ወገኖችን ለማገዝ ዜጎች እንዲረባረቡ ጥሪ አቀረቡ።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ 14ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ፕሬዚዳንቷ ባስተላለፉት መልዕክት፥ “ሃይማኖት የጥንካሬያችን፣ የመቻቻላችን፣ የአብሮ መኖራችን ሚስጥር አንዱ መሆኑን አምናለሁ” ብለዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች መከሰቱን ያነሱት ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ፥ “በተሳካ ሁኔታ የምናድገው የጠፋውን ስናስተካክል ነው” ብለዋል፡፡

የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀያቸው ተመልሰው ኑሯቸውን መምራት እንዲችሉ በቀዳሚነት መላው ኢትዮጵያውያን ሊረባረቡ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ወገን ሲጎዳ ሰብዓዊነት የዕለት ተዕለት ተግባር መሆን አለበት ያሉት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ፥ ለዚህ ተግባርም ሁላችን በአንድነት እንነሳ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

“በእያንዳንዱ ሃይማኖት ተቋማት የህዝብ አገልግሎት መንፈስ መጠናከር ይህን ችግር እንድነወጣ ይረዳናል፤ ምዕመናን ይህን እንዲያጎለብቱ ማድረግ ይገባልም” ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም ሃይማኖታዊ ጉዳዮች የሃይማኖት ሰዎች ሃላፊነት ብቻ መሆኑን አንስተው ፥ የማንም ጣልቃ ገብነት አይጠይቅም ብለዋል፡፡

በሃይማኖት ስም የሚያጋጩ አሉ ያሉት ፕሬዚዳንቷ፥ በሃይማኖቶች መካከል ችግር አለ ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል በሰላም የሚኖርባት ኢትዮጵያን እንድትሆን ሁላችን በጋራ መነሳት አለብን ብለዋል፡፡

በመሰረት አወቀ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.