Fana: At a Speed of Life!

የተጐዱ የሠራዊት አባላትን ለማከም የሚያስችሉ ግብአቶችን ማቅረብ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታችን ነው- ፕ/ር ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ቁሳቁስና የመኪና ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕ/ር ጣሰው ወ/ሃና እንደገለጹት÷ ዩኒቨርስቲው ለመከላከያ ሠራዊት የሕክምና አገልግሎት በግንባርም ሆነ በመከላከያ ሆስፒታሎች ድጋፍ እየሰጠ ነው፡፡
ከእዚህ ሙያው ድጋፍ በተጨማሪም ዛሬ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብ ግምት ያለው ቁሳቁስና የሚኪና ድጋፍ አድርገዋ ብለዋል፡፡
የተጐዱ የሠራዊት አባላትን በቶሎ ማዳንና ማከም የሚያስችሉ ግብአቶችን ማቅረብ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታችንም ነው ብለዋል ፕሮፌሰር ጣሰው፡፡
የሆስፒታሉ አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ተገኝ ለታ በበኩላቸው÷ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድጋ እንዳልተለያቸውና ወደፊትም ከተቋሙ ጋር አብረው እንደሚሰሩ ጠቁመው÷ ለተደረገው ድጋፍ ማመስገናቸውን ከዩኒቨርሲቲው ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.