Fana: At a Speed of Life!

የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ መሰረታዊ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት መንግስት ከተመድ ጋር ለመስራት ዝግጁ ነው – አቶ ደመቀ መኮንን

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኒውዮርክ የስራ ቆይታቸው ጎን ለጎን ከተመድ ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና ጄኔ መሐመድ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ለመገንባት መንግስት በላቀ አጋርነት ከተመድ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።

በዘላቂ ልማት ግቦች አፈፃፀም፣ በሰብዓዊ አገልግሎት ድጋፍ አሰጣጥ እና ወቅታዊ የሃገር ውስጥ ጉዳዮችን በተመለከተ በዝርዝር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ለመገንባት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አቶ ደመቀ ተናግረዋል።

በመሆኑም መንግስት በመልሶ ማቋቋም እና በመልሶ ማልማት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሂደት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በላቀ አጋርነት ከተመድ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አመላክተዋል።

በአሁን ጊዜ ሃገራችንን እየገጠሟት ካሉት የፀጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ የመልሶ ማቋቋም እና የመልሶ ማልማት ተልዕኮን ለማስፈፀም በተመድ በኩል የበለጠ ትብብር እና ድጋፍ እንጠብቃለን ፥ ብለዋል አቶ ደመቀ መኮንን።

በመጨረሻም እስካሁን ድረስ የተመድ በልማት እና ሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት ዙሪያ ለኢትዮጵያ ላበረከተው አስተዋፅዖ በማመስገን፤ በአሁን ጊዜ ወቅቱ የተሻለ ትብብርና መደጋገፍ እንደሚጠይቅ አቶ ደመቀ አስገንዝበዋል።

ምንጭ:- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.