Fana: At a Speed of Life!

የተፈጥሮ ፀጋን በርካሽ በመስጠት በውድ የሚገዛበት ሂደት የሚያበቃበት ዘመን ላይ መድረሳችን አይቀሬ ነው – ኢ/ር ታከለ ኡማ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጉራጌ ዞን የሚገኘውን የሲልከን ማምረቻ ጎብኝተዋል፡፡
ማምረቻው ለሴራሚክ፣ ለብርጭቆ ፋብሪካ፣ ለመስታወት ሥራዎች እና ለተለያዩ ቁሳቁሶች መስሪያነት የሚያገለግል መሆኑ ታውቋል፡፡
ሚኒስትሩ ጉብኝቱን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፥ “ጥሬ እቃ እየላክን ያለቀ እቃ የምንረከብበት ጊዜ የሚያበቃበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም” ብለዋል።
“ባለን ጥሬ እቃ ተጠቅመን እሴት ጨምረን ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የውጪ ምንዛሬ ወጪያችንን አድነን ገቢ የምናገኝበት አቅምን ማሳደግ ላይ እናተኩራለን” በማለትም ተናግረዋል።
በዚህም “እየተከተልነው ያለው መንገድ ይኸው ነው ሲሉም” አመላክተዋል፡፡
የዚህ አይነት ተቋማት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ቢሆንም ሚናቸው ግን ከዚህ ከፍ እንዲል መስራት ይኖርብናልም ነው ያሉት ኢንጂነር ታከለ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.