Fana: At a Speed of Life!

የተፋሰሶች ልማት ባስልጣን የቅድመ ጎርፍ መከላክል ስራዎችን የተመለከተ ውይይት እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተፋሰሶች ልማት ባስልጣን የቅድመ ጎርፍ መከላከል  ስራዎች ሂደትን የተመለከተ ውይይት ከባከለድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ነው።

የተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዳነች ያሬድ÷ የጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን ታሳቢ ያደረገ 600 ሚሊየን ብር መንግስት መድቦ በ7 ክልሎች በ6 የተፋሰስ ቦታዎች ላይ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የጎርፍ መከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰዓት እስካሁን የተሰሩ ስራዎች ምን ላይ ናቸው? ሰኔ 30 ከመድረሱ በፊት ባሉት ቀናት ምን ለመስራት ታስቧል? ባልተሰሩ ስራዎች ላይ አደጋን ለመቀነስስ ምን ይደረጋል? በሚሉ ስራዎች ዙሪያ የኢትዮጵያ ኮንስትራክንሽን ዲዛይንናቁጥጥርና ኮርፖሽን፣ የአማራ፣  የሶማሌ የደቡብ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን ቁጥጥር ኢንተርፕራዝ እየሰሩ ያሉትን ስራዎች ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

በፈተያ አብደላ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.