የቱሉ ቦሎ – ኬላ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ወደ አሰፓልት ንጣፍ ስራ ተሸጋገረ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 80 ኪሎሜትር የሚረዝመው የቱሉ ቦሎ – ኬላ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ወደ አሰፓልት ንጣፍ ስራ መሸጋገሩ ተገለጸ።
እስካሁን ባለው አፈጻጸም 26 ኪሎ ሜትሩ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የፕሮጀክቱን ክፍሎች አስፓልት ለማልበስ እየተሰራ ነው።
በአሁኑ ወቅት የአፈር ቆረጣ ና የአፈር ሙሌት ፣ የቤዝ ኮርስ ስራ ፣ የአስፋልት እና ፣ የድልድይ ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ ነው።
በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የቱሉ ቦሎ – ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት የኦሮሚያ ክልልን ከአጎራባች የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጋር የሚያገናኝ ወሳኝ ፐሮጀክት ነው ተብሏል፡፡
ከቡታጂራ አዲስ አበባ ከሚወስደው አውራ መንገድ ጋርም በአቋራጭ ያስተሳስራል ፡፡
የቱሉ ቦሎ – ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት እየተገነባ የሚገኘው ከመንግስት በተመደበ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በጀት መሆኑ ተመላክቷል።
3 ወረዳዎችን አቋርጦ ኬላ ከተማ የሚደርሰው ይህ መንገድ በአካባቢው በሚገኙ በገብስ ፤ ስንዴ ፤ ባቄላና አተር ምርቶቹ የታወቀ በመሆኑ ምርቶቹን በፍጥነት ወደ ማእከላዊ ገበያ እንዲደርስ ስለሚያስችል ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ያጎለብታል፡፡
የቱሉ ቦሎ – ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት በቀጣይ አመት ለማጠናቀቅ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!