Fana: At a Speed of Life!

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱ ይህንን የገለጹት በቱርክ  የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሃመድ ለፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት ነው ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ሁለቱ አገራት ትብብራቸውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ በመካከላቸው ያሉትን ሰፊ ኢኮኖሚያዊ ፣ ባህላዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ዕድሎች መጠቀም እንዳለባቸውም ገልጸዋል ፡፡

አምባሳደር አደም መሃመድ  በበኩላቸው  በኢትዮጵያ እና በቱርክ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር  እንደሚሰሩ መግለጻቸውን አንካራ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.