Fana: At a Speed of Life!

የቱርክ ቀዳማዊት እመቤት  በአፍሪካ ላይ ያተኮረ መጽሐፋቸውን  አስመረቁ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 11፤ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርክ ቀዳማዊት እመቤት ኤሚኒ ኤርዶጋን ወደ አፍሪካ በመጡበት ወቅት የያዟቸዉን ማስታወሻዎች ያካተተ መጽሐፋቸዉን  ለህዝብ አስተዋውቀዋል፡፡

ቀዳማዊት እመቤቷ  “የአፍሪካ ጉዞዬ ማሰታዎሻዎች”  በሚል ርዕስ ያዘጋጁት መጽሐፋቸው በተመረቀበት ወቅት ባረደረጉት  ንግግር÷ አፍሪካ ከ 2 ሺህ በላይ ቋንቋዎች እና የጎሳ ማህበረሰቦች መገኛ አህጉር መሆኗን ገልጸዋል።

ሀገራቸዉ ቱርክ ከአፍሪካ ጋር የቆየ ወዳጂነት እንዳላት የተናገሩት ቀዳማዊት እመቤት ኤሚሊ ኤርዶጋን፥  በጉዟቸዉ ወቅት ያስተዋሏቸዉ ችግሮች እንዲቀረፉ የቱርክ መንግስት በአጋርነት እንደሚሰራ መግለጻቸዉን ከቱርክ ፕሬዝደንት ጽህፈት ቤት  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የሰላምና ጸጥታ ችግር ፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ፣ የሰብአዊ መብቶች እና የአየር ንብረት ለውጥ በአፍሪካ አህጉር የሚታዩ ችግሮች መሆናቸዉን ተናግረዋል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.