Fana: At a Speed of Life!

የቱርክ ፓርላማ የሀገሪቱ ጦር ወደ ሊቢያ እንዲገባ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቱርክ ፓርላማ የሀገሪቱ ጦር ወደ ሊቢያ እንዲገባ የሚጠይቀውን እቅድ ማፅደቁ ተነገረ።

የቱርክ ጦር ወደ ሊቢያ የሚገባው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና የተሰጠውን የሊቢያ መንግስት ለመደገፍ እንደሆነም ታውቋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና የተሰጠውን የሊቢያ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ፈይዘል አል ሲራጅ እና የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ያጥብ ኤርጎኸን ባሳለፍነው ህዳር ወይ ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ይታወሳል።

መሪዎቹ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ከደረሱባቸው ጉዳዮች ውስጥም የባህር ሀይል፣ የድንበር ጥበቃ እና የደህንነት ትብብር እንደሆነም ተነግሯል።

የቱርክ ፓርላማ የሀገሪቱ ጦር ወደ ሊቢያ እንዲገባ ያፀደቀው እቅድም የስመምነቱ አካል እንደሆነ ነው የተገለፀው።

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ቱርክ በተቻለ ፍጥነት ወታደሮችን ወደ ሊቢያ እንደምትልክ ቀደም ብለው ማስታወቃችውም ይታወሳል።

ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን የጀኔራል ከሊፋ ሃፍታር ወታደሮችን እንቅስቃሴ ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ሃገራቸው ፍላጎት እንዳላት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል።

ምንጭ፦ www.aljazeera.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.