Fana: At a Speed of Life!

የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሰኢድ 57 የህግ ዳኞችን አሰናበቱ

 

አዲስ አበባ፣ግንቦት 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሰኢድ በሙስና እና አሸባሪዎችን በመደገፍ ተሳትፈዋል ያሏቸውን 57 የህግ ዳኞች አሰናብተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር የሀገሪቱ የፍትህ አካላት እራሳቸውን ከተለያዩ ወንጀሎች እንዲያፀዱ እድል ሰጥተው እንደነበር ገለፀዋል፡፡

ፕሬዚደንቱ በቴሌቪዥን ቀርበው ይህን ካሉ ከሰዓታት በኋላ ዳኞቹ በይፋ መባረራቸው በጋዜጣ ታትሞ ወጥቷል ነው የተባለው፡፡

ከተባረሩት ዳኞች መካከል የፍትህ ስርዓቱን ለማስተካከል እንቅስቃሴ ላይ የነበሩት  የከፍተኛ ዳኞች አስተዳደር ምክር ቤት ሃላፊ የሱፍ ቡዛከር ይገኙበታል ተብሏል።

በ2011 የቱኒዚያ አብዮታዊ ዴሞክራሲን ያስተዋወቁት ካይስ ሰዒድ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ጣልቃ እየገቡ ነው በሚል የዳኞች ምክር ቤት ክስ ሲያቀርብባቸው እንደነበር ቲ አር ቲ ወርልድ በዘገባው አስነብቧል፡፡

ሌላኛው ታዋቂ የህግ ዳኛ ቺር አክሬሚም የተባረሩ ሲሆን ዳኛውን አንዳንድ የፖለቲካ አክቲቪስቶች የሀገሪቱ መንግስት ተቃዋሚ ከሆነው ከኤንናህዳ ፓርቲ ጋር ቅርበት አላቸው በሚል ወቀሳ ሲያቀርቡባቸው ነበር ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.