Fana: At a Speed of Life!

የታላቁ የሩጫ ውድድር የሚካሄድባቸው መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አመራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ተጠይቋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ)በነገው ዕለት የታላቁ የሩጫ ውድድር የሚካሄድባቸው መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አመራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሚሽን ጠይቋል፡፡

ፖሊስ የሚያደርገውን  የፀጥታ ዝግጅት በቀና መንፈስ በመተባበር የሚታወቀው መላው የመዲናዋ ነዋሪ እና የውድድሩ ተሳታፊዎች ለፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በዕለቱ መነሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ የሚጀመረው ወድድር በአዲስ አበባ ስታዲዮም ሜክሲኮ አደባባይ በልደታ ቤተክርስቲያን በማድረግ በዛጉዌ ህንፃ በመታጠፍ-በጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ በፍልውሃ በመድረግ በካዛንቺስ በኡራኤል ቤተክርስቲያን የአትላስ መንገድ በመያዝ አክሱም ህንፃ አጠገብ መድረሻውን እንደሚያደርግ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

በመሆኑም የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር

-ኮቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበልህንፃ

-ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ የቀድሞ አራተኛ ክፍልጦር

-ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው ኬኬ ህንፃ ወይም ጨርቆስ ማዞሪያ

-ከሳር ቤት ወደሜክሲኮ ለሚመጡ አፍሪካ ህብረት አደባባይ

-ከካርል አደባባይ ወደከፍተኛ ፍ/ቤትየሚወስደውመንገድ ልደታ ፀበል

-ከጦርኃይሎች ወደ ሚክሲኮ ለሚመጡ ኮካ መገንጠያ  ሜክሲኮ ለሚመጡ ጆስሐንሰን

– ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ በርበሬበረንዳ

ከተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በጎማ ቁጠባ የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር (ሼልድሬንስ)

-ከቸርቸር ወደ አምባሳደር ፣ ሜክሲኮ እና ለገሃር ለሚመጡ ቴድሮስአደባባይ

-ከአዋሬ ወደ ካዛንቺስ ለሚመጡ ሴቶች አደባባይ-  ከመገናኛ ወደ 22 ለሚመጡ ዘሪሁን ህንፃ

-ከቦሌ መድኃኒያለም የሚመጡ አትላስ ሆቴል አካባቢ

ለተሽከርካሪ ዝግ ሲሆኑ በተጨማሪም ከውስጥ ለውስጥ መንገዶች ተወዳዳሪዎቹ ወደሚያልፉባቸው መንገዶች መውጣት በጥብቅ የተከለከለ በመሆኑ አሽከርካሪዎች ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙና ለፀጥታ አካላት ተባባሪ እንዲሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ በተጨማሪም ወድድሩ በሚካሄድባቸው መንገዶች ከማለዳው 11 ሰዓት ከ 30  ጀምሮ ተሸከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥም ሆነ ለፖሊስ መረጃ ለመስጠት 011-1-11-01 11እና በ991 ነፃ የስልክ ቁጥሮች መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽን ያሳውቃል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.