Fana: At a Speed of Life!

የታንዛኒያን ድንበር በህገወጥ መልኩ አቋርጠው የገቡ 1 ሺህ 100 ኢትዮጵያውያን እስር ላይ እንደሚገኙ ኤምባሲው ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታንዛኒያን ድንበር በህገወጥ መልኩ አቋርጠው የገቡ 1 ሺህ 100 ኢትዮጵያውያን እስር ላይ እንደሚገኙ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።

ኤምባሲው ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ በታንዛኒያ አራት ግዛቶች ውስጥ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ባደረገው ጉብኝት 1 ሺህ 100 ኢትዮጵያውያን ታስረው ማግኘቱን ገልጿል።

የታንዛኒያን ድንበር በህገወጥ መልኩ አቋርጠው በመግባታቸው በፖሊስ ተይዘው ከ6 ወር እስከ 2 አመት የሚደርስ የእስራት ፍርድ የተፈረደባቸው ናቸው ተብሏል።

ታሳሪዎቹ በጾታ ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ እድሜያቸው ከ14 እስከ 46 አመት ባለው ውስጥ የሚገኙ ናቸው ብሏል ኤምባሲው።

ከታሳሪዎቹ ጋር አብረዋቸው ጉዞ ጀምረው የነበሩት በርካቶች በመንገድ ላይ ከአጠገባቸው በሞት የተለዩያቸው መሆኑም ተነግሯል።

በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሀገራት የድንበር ቁጥጥራቸውን አላልተዋል በሚል በደላሎች ተታለው ለስደት የተዳረጉ መሆኑን  ታሳሪዎቹ ለኤምባሲው አስታውቀዋል።

እንዲሁም  ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት ተቋማት እና የቤተ እምነት አባቶች  ጸሎት እና ምርቃት በማድረግ አበረታተው እየሸኟቸው መሆኑን ታሳሪዎቹ ተናግረዋል።

ኤምባሲው ህገወጥ ስደትን ለመከላከል የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን በአግባቡ የማይወጡ ከሆነ የዜጎችን ስቃይ እና እንግልት እንዲሁም ሞት ማስቆም አይቻልም ብሏል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.