Fana: At a Speed of Life!

የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምርት የሚጀምርበት ቀን ነገ ይገለፃል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና የክልሎች ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች በቀጣይ የትምህርት ሁኔታ ላይ ዛሬ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ውይይቱ ነገም ቀጥሎ የሚውል ሲሆን በውይይታቸውም በቀጣይ የትምህርት ሁኔታ ላይ ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ነው የተባለው።
በዚህም መደበኛ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን፣ የ8ኛና 12ኛ ክፍል ክልላዊ እና ሀገራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን እንዲሁም በግል ትምህርት ቤቶች ላይ እየቀረቡ ያሉ ቅሬታዎችን ውሳኔ ከሚተላለፍባቸው ጉዳዮች መካከል ይገኛሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪም አዲሱ የትምህርት ስርዓት ዝግጅት አካሄድ እና ሁኔታ በውይይቱ ላይ የሚገመገም ሲሆን ውሳኔ ይሰጥበታል ተብሎም ይጠበቃል።
እንዲሁም የጎልማሶች ትምህርት አሰጣጥና አፈፃፀምም በውይይቱ ውሳኔ ከሚያገኙ ጉዳዮች መካከል መሆኑ ታውቋል።
በውይይቱ ላይ የተደረሰው ውሳኔም በነገው እለት ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.