Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ብርሃን ምዘና ፈተና ከመጋቢት 15 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ብርሃን ምዘና ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመጋቢት 15 ጀምሮ ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ምዘናው በሚሰጥበት ሁኔታ ላይ ከየክልሉ ከተውጣጡ የጎላማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ጋር ምክክር እያካሄደ ይገኛል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር  ዴኤታ  ዶክተር ጌታሁን ጋረደው ምዘናው እንደ ሀገር የተማረ የሰው ሃይልን ለመለየት የሚያስችል  መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተለያየ መንገድ ተምረው ማንበብ፣ መፃፍና ማስላት የሚችሉ ጎልማሶች ሁሉ በምዘናው እንዲካተቱ እንደሚደረግም ነው ያስረዱት፡፡

የምዘና ፈተናው ጎልማሶቹ ማንበብ መፃፍና ማስላት በሚችሉበት ቋንቋ የሚዘጋጅ መሆኑም ነው የተነገረው።

በምዘናው 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ከ3ኛ ክፍል ወደ 4ኛ ክፍል መዘዋወራቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት እንደሚሰጥም ሚኒስትር ዴኤታው መናገራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.