Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ብቃት ማዕቀፉ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን መፍታትን ታሳቢ አድርጎ መዘጋጀት እንዳለበት ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የትምህርት ብቃት ማዕቀፍ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን መፍታትን ታሳቢ አድርጎ መዘጋጀት እንዳለበት ተጠቆመ፡፡
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ቀጠናዊ ትሥሥር ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና የኢትዮጵያ የትምህርት ብቃት ማዕቀፍ ዝግጅት ላይ ትኩረቱን ያደረገ የምክክር መድረክ እተካሄደ ነው፡፡
የመንግስት አስፈፃሚ አካላት እንደ አዲስ መደራጀታቸውን ተከትሎ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከክህሎት ልማቱ አኳያ ያለውን የብቃት ማዕቀፍ ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመወያየት ታሳቢ ተደርጎ ነው መድረኩ የተዘጋጀው፡፡
ጥራትና አግባብነት፣ ተደራሽነትና ፍትሃዊነት እንዲሁም ተጠያቂነትና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ያሉ ፈታኝ ችግሮች መሆናቸው እና እንደ አገር በትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የብቃት ማዕቀፉ ፋይዳው የላቀ መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል፡፡
ከዚህ ቀደም በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የብቃት ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ሲደረግ እንደቆየ እና ማዕቀፉ እንደ አገር በሚመለከተው አካል ያልፀደቀ በመሆኑ እስከ አሁን ድረስ በዘርፉ ችግር ሆኖ መዝለቁም ተመላክቷል፡፡
የምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ቀጠናዊ ትሥሥር ፕሮጀክት በሴክተሩ ካሉት ሥራዎች በተጨማሪ የኢትዮጵያ የትምህርት ብቃት ማዕቀፉን የማጠናቀቅ ኃላፊነትን ወስዶ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆቱ እና በዚህም በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በፌዴራል ደረጃ ቴክኒክ ቡድን በማዋቀር የተሻሻለውን የቴክኒክና ሙያና ሥልጠና ፖሊሲ መሠረት በማድረግ ሰነዱ ለውጡንና ወቅቱን የዋጀ እንዲሆን ጥረት እንደተደረገ ነውም ተብሏል፡፡
ሰነዱ በምሥራቅ አፍሪካ ከሚገኙ አገራትና ከቀጠናው የቴክኒክና ሙያ ብቃት ማዕቀፍ ጋር የሚናበብና የሚጣጣም እንዲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንና በተለይ ከኬንያ እና ታንዛኒያ ጋር በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.