Fana: At a Speed of Life!

የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና ዲፒ ወርልድ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስቴርና ዲፒ ወርልድ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
በዚህ ስምምነት መሠረት ዲፒ ወርልድ የተሰኘው ኩባንያ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የበርበራ ኮሪደርን ለማልማት የ1 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ይፈጽማል ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ማከማቻ መጋዝኖችን በተለያዩ የትራንስፖርት ማጓጓዣ አማራጮች ማስፋት ላይ እንደሚሠራ ተገልጿል።
የገቢ እና ወጪ ንግድን ለማሳለጥ የጅቡቲ ወደብን አማራጭ ለማሳደግ እንደሚያግዝም የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊ ሞገስ ተናግረዋል።
በቀጣይም የኢትዮጵያን የሎጂስቲክ ሥርዓት ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሠራም መገለጹን ኢቢሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
May be an image of 2 people and people sitting
0
People Reached
22
Engagements
Boost Post
19
1 Comment
2 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.