Fana: At a Speed of Life!

የትራንስ ኢትዮጵያ ንብረት የሆኑ ለስራ ወደ ጂቡቲ የተጓዙ 179 የደረቅ ጭነት ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን ለመመለስ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከታገዱት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የትራንስ ኢትዮጵያ ንብረት የሆኑ ለስራ ወደ ጂቡቲ የተጓዙ እና ወደ ሀገር ቤት ሳይመለሱ የቀሩ 179 የደረቅ ጭነት ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን እና አራት የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ /ቦቴ/ ከጅቡቲ ለመመለስ ውይይት ተካሄደ፡፡

 

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እነዚህ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ እና የህዝብን ጥቅም ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ጂቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ከጂቡቲ መንግስት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ዐቃቤ ህግ እና የፖሊስ ተቋማት የበላይ አመራሮች ጋር የተሳከ ውይይት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ተሽከርካሪዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ቤት እስከሚመለሱ ድረስ የኢትዮጵያ መንግስት ከጂቡቲ መንግስት ጋር በመተባበር ጠንካራ ጥበቃ እያደረገላቸው መሆኑን በውይይቱ የተሳተፉት የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በወንጀል የተገኙ ሃብቶች ማስመለስ ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ አለም አንተ አግደው ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም ወደ ሀገር ለመመለስ የተደረገው ጥረት ከህዝብ አገልጋይነት ስሜት በተቃረነ ሁኔታ የህወሓት አባል እና የቀድሞ ታጋይ የነበሩት የተሽከርካሪዎቹ ሾፌሮች ተሽከርካሪዎቹን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆን ተልዕኮው እንዳይሳካ ጥረት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ሆኖም ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና ጂቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከጂቡቲ መንግስት ጋር በጋራ በመሆን ተሽከርካሪዎቹን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ተገቢውን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ባለፈው ወር ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በተለያዩ የወንጀል ተግባር ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል በተጠረጠሩ ድርጅቶች ላይ የንብረት እገዳ እንዲጣል ማድረጉ ይታወሳል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.