Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ሕዝብ ከገጠመው ችግር እንዲወጣ የአፋር ሕዝብ ከጎናችን አልተለየም – ዶክተር ሙሉ ነጋ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ሕዝብ ከገጠመው ችግር እንዲወጣ የአፋር ሕዝብ ሁልጊዜም ከጎኑ አለመለየቱን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ገለፁ፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው የአፋር ክልል ሕዝቦች በትግራይ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ያበረከቱትን ድጋፍ ተቀብለዋል።

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ሕዝብ ከዘጠኝ ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኤለማ አቡበከርና የአፋርን ሕዝብ የወከሉ የሃገር ሽማግሌዎች መቐለ ተገኝተው አስረክበዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ የአፋርና የትግራይ ሕዝቦች በደምና በታሪክም የተሳሰሩ፣ መቼም መለያየት የማይችሉ ናቸው ብለዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ ከገጠመው ችግር እንዲወጣ ሁልጊዜም ከጎናቸው ያልተለዩ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

የዛሬው ድጋፍም የአፋር ሕዝብ ለትግራይ ሕዝብ ያለውን አለኝታነት የገለጸበት መሆኑን ነው የተናገሩት።

የሁለቱ ሕዝቦች ወንድማማችነትና ትስስር ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚጎለብት መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

ድጋፉ የመልካም ጉርብትና መገለጫ መሆኑን በመጥቀስ የአፋርን ሕዝብና መንግስት አመስግነዋል፡፡

የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኤለማ አቡበከር በበኩላቸው የአፋርና የትግራይ ሕዝቦች በአኗኗርና በኑሮ ዘይቤ ይመሳሰላሉ ብለዋል፡፡

ሁለቱ ሕዝቦች ችግሮችና መልካም አጋጣሚዎችን በጋራ ያሳለፉ መሆናቸውን በማውሳት የትግራይ ሕዝብ ለደረሰበት ጉዳት ከ2 ሺህ 700 ኩንታል በላይ የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የኦሮሚያና የደቡብ ክልሎች እንዲሁም የአዲስ አበባ አስተዳደር በትግራይ ለተጎዱ ወገኞች ድጋፍ ማድረጋቸውን ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.