Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የአዲግራት ከተማን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ እና የጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በአዲግራት ከተማ የህወሓት ጁንታ ያደረሰውን ጉዳት ጎብኝተዋል፡፡

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እና በትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ የተመራ ልዑክ በአዲግራት ዩኒቨርሲቲና በአዲስ መድሃኒት ፋብሪካ ላይ የደረሰውን ውድመት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ የህወሓት ጁንታ ለህዝብ የማያስብ እና ከህዝብ አብራክ የወጣ የማይመስል የጥፋት ቡድን መሆኑን በመሰረተ ልማቶች ላይ ባደረሰው ጥፋት ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

የህወሓት ጁንታ በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ዝርፊያ ከመፈጸም አልፎ የቀረው ንብረት ለመጭው ትውልድ እንዳያገለግል ሰባብሮ እና ከጥቅም ውጭ አድርጎ መፈርጠጡም ተነግሯል።

በአዲግራት ከተማ በሚገኘው አዲስ መድሃኒት ፋብሪካም ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸሙ ተገልጿል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዶክተር ሙሉ ነጋ÷ ቡድኑ በህዝብና በመንግስት ንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ማድረሱን ጠቁመዋል፡፡

የቡድኑ የህገወጥ ድርጊት ሰለባ የነበረችው የአዲግራት ከተማ ሰላም በአሁኑ ወቅት እየተመለሰ እንደሆነም ተናግረዋል።

በቀጣይ በትግራይ ክልል አጠቃላይ በህወሓት ጁንታ የደረሱ ጉዳቶች ተጠንተው ለፌደራል መንግስት ቀርበው መፍትሄ እንዲያገኙ ይደረጋልም ነው ያሉት።

የጉብኝት ልዑኩ የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅና የፈረሰውን የመንግስት መዋቅር መልሶ ለማቋቋም ከአዲግራት ከተማ ወጣቶች ጋር ምክክር አድርጓል።

በምክክር መድረኩ በጋራ ለመስራት የሚያስችል መግባባት ላይ መደረሱን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.