Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክልል ባቀረበው ፍላጎት መሠረት የአፈር ማዳበሪያ መቶ በመቶ እንዲቀርብ መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የትግራይ ክልል ባቀረበው ፍላጎት መሠረት የአፈር ማዳበሪያ መቶ በመቶ እንዲቀርብ መደረጉ ተገልጿል።

በክልሉ ለሚገኙ አርሶ አደሮች ልዩ ትኩረት በመስጠት በዘር ወቅት የሚያስፈልጉ የግብርና ግብዓቶች በበቂ መጠን እየቀረቡ መሆኑ ተገለጸ።

በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ግብዓትና ግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ተስፋ እንደገለጹት፤ ክልሉ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የግብርናውን ሥራ ለማስቀጠል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው።

በተለይም አርሶ አደሩ በዘር ወቅት የሚያስፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ መቶ በመቶ ግዢው ተጠናቅቆ ለክልሉ ተደራሽ ሆኗል።

የትግራይ ክልልን ጨምሮ በአገሪቱ በሚገኙ በሁሉም ክልሎች የግብርና ግብዓቶችን በወቅቱና በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፤ በተያዘው በጀት ዓመት ከሁሉም ክልሎች በተሰበሰበው ፍላጎት 18ነጥብ 1ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እንደሚያስፈልግ ማወቅ ተችሏል።

ከዚህም ውስጥ ትግራይ ክልል 8መቶ ሺህ ኩንታል ያስፈልገኛል ብሎ ባቀረበው ፍላጎት መሠረት በልዩ ሁኔታ መቶ በመቶ እንዲቀርብ መሆኑን ኢፕድ ዘግቧል።

በ2012 ዓ.ም ወደ ክልሉ ገብቶ ጥቅም ላይ ያልዋለ 214 ሺህ 867 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያን ጨምሮ በተያዘው በጀት ዓመት ከተገዛው ደግሞ 225ሺህ 325 ኩንታል በድምሩ 440ሺህ 169 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለክልሉ የቀረበ መሆኑን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.