Fana: At a Speed of Life!

የቶኪዮ ኦሊምፒክ ለሌላ ጊዜ እንዲዛወር በጃፓንና በዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ላይ ጫናው በርትቷል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ውድድር ለሌላ ጊዜ እንዲዛወር በአስተናጋጇ ሀገር ጃፓንና በዓለም ኦሊምፒክ ኮሚቴ ላይ ጫናው በርትቷል።

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ካናዳ በውድድሩ እንደማትሳተፍ ማስታወቋን ተከትሎ በርካቶች ውድድሩ ሌላ ጊዜ እንዲዛወር እየጠየቁ ነው።

ካናዳ ከአትሌቶቿ ጤና የሚበልጥ ነገር እንደሌላ በማሳወቅ ነው ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ የሚካሄድ ከሆነ እንደማትሳተፍ ያስታወቀችው።

የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በዛሬው እለት ውድድሩ ከዚህ ቀደም ሲካሄድ በነበረው ልክ መካሄድ የማይችል ከሆነ ለሌላ ጊዜ ይዛወራል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውድድርን ሙሉ በሙሉ መሰረዝ አማራጭ እንዳልሆነ እና የሚሻለው ለሌላ ጊዜ ማዛወር መሆኑንም ነው ያመለከቱት።

በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ስብሰባውን ያደረገው የዓለም ኦሊምፒክ ኮሚቴ በፈረንጆቹ የፊታችን ሀምሌ 24 እንዲጀመር ቀን ተቆርጦለት የነበረው ውድድር ምናልባትም ለሌላ ጊዜ ሊዛወር የሚችልበትን ሁኔታ እየተመለከተ መሆኑንም አስታውቋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.