Fana: At a Speed of Life!

የቻይናዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል

አዲስ ፣አበባ  ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) የቻይናዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት  አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን  አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ እና ሌሎች አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከአውሮፓውያኑ 1970 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ይፋዊ የዲፕሎማሲ ግኑኝነት የጀመሩት ኢትዮጵያና ቻይና አሁን ላይ በንግድ እና ኢንቨስትመንት እንዲሁም ዲፕሎማሲ ጠንካራ ግኑኝነት መመስረት ችለዋል።

በአውሮፓውያኑ ከ2016 እስከ 2018 መካከልም ኢትዮጵያ ከቻይና ያገኘችው ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ወደ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር  ይጠጋል።

በቻይና መንግስት ቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሽዬቲቭም በኩልም ኢትዮጵያ ለአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር ዝርጋታ እና ለአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ከቤጂንግ የብድር ድጋፍ አግኝታለች።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤትም ቻይና የኢትዮጵያን እውነት በመረዳት ድምፅ በመሆን ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ስታደርግም ቆይታለች።

 

በፍሬህይወት ሰፊውና አወል አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.