Fana: At a Speed of Life!

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲሱ አመት ጉዟቸው አፍሪካን ይጎበኛሉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በፈረንጆቹ አዲስ አመት የመጀመሪያ ጉዟቸው አፍሪካን እንደሚጎበኙ አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሩ ከፈረንጆቹ ጥር 4 እስከ 7 በኤርትራ፣ ኬንያ እና ኮሞሮስ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዣኦ ሌጂያን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በማልዲቭስ እና ስሪላንካ ጉብኝት ያደርጋሉ ነው የተባለው።

የቻይና አፍሪካ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ፥ የቻይና በአፍሪካ የኢንቨስትመንት እና በሌሎች እንቅስቃሴዎች ላይ ያላት ተሳትፎ እያደገ መምጣቱ ይታወቃል፡፡

በቅርቡ በተካሄደው የቻይና አፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ፎረም ላይ ቻይና እና አፍሪካ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተያያዘ ስራዎችን ለመስራት መስማማታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አስታውሷል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.