Fana: At a Speed of Life!

የቻይና መንግስት 400 ሺህ ዶላር የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና መንግስት የጨቅላ ህፃናት ሞት ለመከላከል የሚያስችል 400 ሺህ ዶላር የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁሶች ለጤና ሚኒስቴር አስረክቧል።
እርዳታው የቻይና መንግስት በትግራይ እና በደቡብ ክልሎች የሚገኙ ሁለት ዞኖች ውስጥ የጨቅላ ህፃናት ጤና ለማሻሻል እና ሞት ለመቀነስ እንዲሁም የጤና ተቋማትን ለማስፋፋት ከያዘው የ1 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ውስጥ የሚካተት ነው ተብሏል።

የእርዳታው ቁሳቁሶች የሚሰጡት ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች  ፣ጤና ጣቢያዎች ና ጤናኬላዎች መሆኑ ታውቋል፡፡

ቁሳቁሶቹ የተገዙትም በዩኒሴፍ አማካኝነት ሲሆን ዩኒሴፍ በፕሮጀክቱ ለጤና ባለሙያዎች ስልጠናም እንደሚሰጥም ተጠቅሷል።

እርዳታውን የተረከቡት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ5 ዓመት በታች የሆኑት የህጻናትን ሞት በመቀነስ የምዕተዓመቱን የልማት ግብ ማሳካት የቻለች ቢሆንም የጨቅላ ህፃናትን ሞት በተፈለገው መጠን ባለመቀነሱ የጤናው ዘርፍ ትልቅ የትኩረት አጀንዳ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሯ ለተደረገው ድጋፍ ለቻይና መንግስትንና ለዩኒሴፍ ምስጋና አቅርበው ሌሎች አካላት ተጨማሪ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.