Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ሮኬት ግዙፍ አካል ከህዋ ወደ መሬት ይወድቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና ሎንግ ማርች 5ቢ የተሰኘው ሮኬት አካል ከህዋ ወደ መሬት በፍጥነት እየተምዘገዘገ መሆኑ ተነግሯል።

መሬት ላይ ሲወድቅ የት አካባቢ ሊያርፍ ይችላል የሚለው ጉዳይ ብዙዎችን እያሳሰበ የሚገኝ ሲሆን በተያዘው ሳምንት ምድር ላይ እንደሚያርፍ ነው የሚጠበቀው።

ይህ የሮኬት አካል ወደ ታችኛው የአየር ንፍቀ ክበብ ለመግባት በመሬት ዙሪያ እየተሽከረከረ እንደሚገኝ ቢቢሲ ዘግቧል።

አሜሪካ የዚህን ሮኬት አካል ጉዞ እየተመለከተች መሆኑን ብትገልፅም መትታ የመጣል እቅድ እንደሌላት ገልፃለች።

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን የሮኬቱ አካል ማንንም የማይጎዳበት ስፍራ ያርፋል ብለን ተስፋ እናደርጋልን፤ይህም ውቅያኖስ ወይም ሌላ ስፍራ ሊሆን ይችላል ሲሉ ነው የገለፁት።

የቻይና መገናኛ ብዙሃን ባለፉት ቀናት የሮኬቱ አካል ሰዎች በማይኖሩበት አካባቢ ይወድቃል የሚለውን ሃሳብ ውድቅ ሲያደርጉ እንደነበረ ተጠቁሟል።

መገናኛ ብዙሃኑ የሮኬቱ አካል ወደ ዓለም አቀፍ የውሃ አካል እንደሚወድቅ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.