Fana: At a Speed of Life!

የቻይና-አሜሪካ አለመግባባት ምሥራቃዊ አፍሪካን ይበልጥ ወደ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሊመራው ይችላል እየተባለ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በታይዋን ጉዳይ ላይ በቻይና እና በአሜሪካ መካከል የተጀመረው አለመግባባት ምሥራቃዊ አፍሪካን የበለጠ ወደ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ ሊያስገባው ይችላል እየተባለ ነው።

ከኮቪድ -19 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማገገም በመታገል ላይ ባለችው አፍሪካ በሩሲያ ዩክሬን ግጭት ምክንያት መሠረታዊ ሸቀጦች ላይ የዋጋ መናር ይስተዋላል።

ቻይና እና አሜሪካ በታይዋን ጉዳይ ላይ ሌላ አለመግባባት ውስጥ መግባታቸው ደግሞ በተፋላሚዎቹ ሀገራት ሰበብ ሀገራቱን ጨምሮ ምዕራባውያን ለአፍሪካ ትኩረት እንዲነፍጉ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ዘ ኢስት አፍሪካን አስነብቧል፡፡

ቻይና የታይዋንን ሸቀጦች አግዳለሁ ማለቷ ደግሞ በተለይ ከታይዋን በወጪንግድ የሚወጡ ከፊል አስተላላፊ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ማሻቀብ ሊያስከትል እንደሚችልም ተዘግቧል፡፡

እንደሚታወቀው ታይዋን ቀድሞም ቢሆን በዓለም ከፍተኛ እጥረት አለ የሚባልለትን እና እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የ “ሴሚኮንዳክተር ቺፕ” ትልቋ አምራች ሀገር ናት፡፡

ቻይና ደግሞ ታይዋን ግዛቴ ናት በሚል ለማስመለስ ወታደራዊ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምራለች፡፡

አሜሪካም ታይዋን ለምን ተጠቃች በሚል ሰበብ ቻይና ላይ ወታደራዊ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ጆ ባይደን ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡

በዚህም አለ በዚያ ቻይናም ሆነች አሜሪካ ጦርነቱ ሁለቱንም ወገኖች እንደሚጎዳና ከቁጥጥር ውጪ ሊሆን እንደሚችልም ባለሙያዎች ይናገራሉ።

አሁን ላይ እውነታው አፍሪካን በዘነጋው የኃያላኑ ሀገራት ፍጥጫ የአኅጉሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕጣ ፋንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ከኃያላኑ በኩል የተባለ ነገር የለም፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.