Fana: At a Speed of Life!

የቻይና- አፍሪካ ወዳጅነት እና ትብብር ተጠናክሮ ይቀጥላል -ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና- አፍሪካ ወዳጅነት እና ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ አስታወቁ፡

የቻይና – አፍሪካ 8ኛው የሚኒስትሮች ጉባኤ በሴኔጋል ዳካር እየተካሄደው ነው፡፡

በጉባኤው የቻይና እና የአፍሪካ ወዳጅነት በንግድ፣ በታዳሽ ኃይል እና በክትባት አቅርቦት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ተናግረዋል፡፡፡

ቻይና ከአፍሪካ ድህነትን ለመቀነስ እና በግብርናው ዘርፍ ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ 10 ፕሮጀክቶችን ቀርጻ እንደምትሰራ ነው ፕሬዚዳንቱ የገለጹት፡፡

በበይነ መረብ እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ሀገራት እና ቻይና ጥልቅ ወዳጅነት ያላቸው መሆኑን ፕሬዚዳንት ሺ አስረድተዋል፡፡

ሀገራቱ በቀጣይ በሚኖራቸው የትብብር አቅጣጫዎች ላይ በተለይም በልማት፣ ኮሮና ወረርሽኝን መግታት፣ በአረንጓዴ ልማትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ መሠራት በሚገባቸው ስራዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ሺ ቻይና ለአፍሪካ ሀገራት ቀደም ብሎ ከለገሰችው የኮቪድ 19 ክትባት በተጨማሪ 1 ቢሊየን ዶዝ እንደምታቀርብም ተናግረዋል፡፡

በወረርሽኙ ቻይና አጣብቂኝ ውስጥ በገባችበት ጊዜ የአፍሪካ ሀገራት እና የአፍሪካ ሕብረት የሰጡንን ጠንካራ ድጋፍ መቼም አንዘነጋውም ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፡፡

ቻይና ለአፍሪካ 10 የሕክምናና የጤና ፕሮጀክቶችን ቀርጻ 1 ሺህ 500 የሕክምናና የኅብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች ቡድን ወደ አፍሪካ እንደምትልክም ጠቁመዋል፡፡

 

ምንጭ÷ ሲጂቲ ኤን

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.