Fana: At a Speed of Life!

ለትምህርት ሚኒስቴር 500 ሺህ ማስክና 11 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2013  (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የቻይና የንግድ ምክር ቤት ለትምህርት ሚኒስቴር 500 ሺህ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብልና  11 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎችን ድጋፍ አድርጓል።

የቻይና የንግድ ምክር ቤት ለትምህርት ሚኒስቴር የኮቪድ 19 መከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገው ዳግም በተከፈቱ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የተደረገ ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር  ጌታሁን መኩሪያ ከቻይና ኢምባሲ የኢኮኖሚና ንግድ ጉዳዮች አማካሪ ሊዩ ዩና የካምፓኒ ተወካዮች ቁሳቁሶቹን ተረክበዋል።

ድጋፉ 500ሺህ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብልና 11ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎች ናቸው።

በዚሁ ወቅት ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ድጋፉ የኮሮና ቫይረስን በመከላከል የተጀመረውን የመማር ማስተማር ስራ በማገዝ ተማሪዎች ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠበቁ ያግዛል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በምታደረገው ጥረት ውስጥ የቻይና መንግስትና የንግድ ማህበረሰብ ድጋፍ ከፍተኛ ነው ያሉት ሚኒስትሩ÷ የቻይና የንግድ ምክር ቤት ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

የቻይና ኢምባሲ የኢኮኖሚና ንግድ ጉዳዮች አማካሪ ሊዩ ዩ÷ የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ጀምሮ የቻይና መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።

በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና የንግድ ምክር ቤት አምቡላንሶችንና አጋዥ የመተንፈቫ መሳሪያዎችን ጨምሮ በሀገር ውስጥ የህክምና መሳሪያዎች እንዲመረቱ ለኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ ሲያደርግ  መቆየቱን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.