Fana: At a Speed of Life!

የቻይና የጠፈር ተመራማሪዎች ህዋ ላይ ማስተማር ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና የጠፈር ተመራማሪዎች ህዋ ላይ ማስተማር ጀመሩ።

የጠፈር ተመራማሪዎቹ ክብደት የሌለው አካባቢ በቁሶች እና በኦፕቲክስ እንቅስቃሴ ላይ ያለውን ተጽእኖ በሚመለከት የፊዚክስ ትምህርት በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ አድርሰዋል፡፡

ጠፈርተኞቹ በትናንትናው እለት በቀጥታ ስርጭት የሠጡት የፊዚክስ ትምህርት ክብደት የሌለው አካባቢ የቁሶችን እና ኦፕቲክስ እንቅስቃሴን እንዴት እንደሚጎዳ ለማሳየት ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የቤጂንግ እና ከፊል የራስ ገዝ አስተዳደር የሆነችውን ሆንግ ኮንግን ጨምሮ ከአምስት ከተሞች የተውጣጡ ተማሪዎች ህዋ ላይ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ በተመለከተ እንዲያብራሩላቸው ለጠፈርተኞቹ ጥያቄ በማቅረባቸው በጠፈርተኞቹ የጣቢያውን ሁለንተናዊ ገጽታ የሚያሳይ ምናባዊ ገለጻ እንደተደረገላቸው በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

በጠፈር የምርምር ጣቢያው ላይ ብቸኛዋ ሴት ዋንግ ያፒንግ በዋና አስተማሪነት ሚና፣ ዬ ጓንግፉ ደግሞ ረዳት እና ዋና አዛዥነት ሚናውን የተወጡ ሲሆን ዣይ ዚጋንግ ደግሞ የካሜራ ቀረጻ ስራውን በመስራት ትምህርታዊ የቀጥታ ስርጭቱን ወደ አየር እንዲበቃ ማድረጋቸውን የቲአርቲ ዘገባ ያስረዳል፡፡

ይህች ብቸኛዋ ቻይናዊት የጠፈር ተመራማሪ ዋንግ ያፒንግ በ2013 እ.ኤ.አ ከቻይና ቀደምት የሙከራ ጣቢያዎች በአንዱ ላይ ተመሳሳይ ትምህርት አስተምራ እንደነበር በዘገባው ተዳሷል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.