Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ጦር በታይዋን ደሴት ዙሪያ ጥምር ወታደራዊ ልምምድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ጦር ምስራቃዊ ዕዝ በታይዋን ደሴት ዙሪያ ወታደራዊ ልምምድ መጀመሩ ተሰምቷል፡፡

ወታደራዊ ልምምዱ የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት ተከትሎ የተጀመረ መሆኑም ነው የተገለጸው።

የምስራቃዊ ዕዝ ዋና አዛዥ እንደገለፁት ልምምዱ በሰሜን ፣ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ ምስራቅ የታይዋን ደሴቶች ላይ እየተደረገ ሲሆን የወታደራዊ እዙ የባህር ሃይል፣ የአየር ሃይል እና የስትራቴጂክ ድጋፍ ሃይል በልምምዱ ተሳታፊ ናቸው።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ዋንግ ይ የፔሎሲ ጉዞ የአንድ ቻይናን መርህ እና የሶስቱን የቻይና አሜሪካ ድንጋጌዎች የሚጥስ መሆኑን በሰጡት መግለጫ አመላክተዋል፡፡

ቻይና በታይዋን ጉዳይ ያስቀመጠችው  ቀይ መስመር መጣሱን ተከትሎ ቻይና ተመጣጣኝ አፀፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ መናገራቸውን አር ቲ እና ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግበዋል።

ታይዋን በበኩሏ ቻይና የአየር እና የባህር በሮችን ዘግታብኛለች ስትል ወቀሳ እያቀረበች ነው፡፡

የታይዋን የመከላከያ ባለስልጣናት እንደገለጹት ቤጂንግ የደሴቲቱን የውሃ እና የአየር ክልል ለመውረር ተዘጋጅታለች በማለት ቻይናንን እየከሰሱ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.