Fana: At a Speed of Life!

የኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን በሐመር እና በናፀማይ ወረዳዎች ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን በደቡብ ኦሞ ዞን በሐመር እና በናፀማይ ወረዳ የሴቶችን የትምህርት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደጊያ ፕሮጀክትን የፋውንዴሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ወይዘሮ ሮማን በመርሐ ግብሩ ÷ለሴት ተማሪዎች የማጣቀሻ መጽሐፍትና ሌሎች ግብዓቶችን በስጦታ መልክ ያበረከቱ ሲሆን÷ የሴት ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት አሰጣጥ ሁኔታን በመጎብኘት ከተማሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ተማሪዎች በዕውቀት ወደ ተሻለ ደረጃ ለመድረስ በርትተው መማር እንዳለባቸው እና ወንዶችም ሴቶችን መደገፍ እንዳለባቸው ምክራቸውን ለግሰዋል።

በቀጣይ በሁለቱ ወረዳዎች የሴቶች የትምህርት ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲያድግ ከመንግስት ጎን በመቆም ድጋፍ እንደሚያደርጉ የፋውንዴሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሮማን መናገራቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡

የደቡብ ኦሞ ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ወሊ ሀይሌ እንደ ዞን ከ52 ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመው÷ ስለሚደረገው ድጋፍ በዞኑ ትምህርት መምሪያ ስም ለኃይለማሪያምና ለሮማን ፋውንዴሽን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.