Fana: At a Speed of Life!

የኔዘርላንድስ ፖሊስ በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር አዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኔዘርላንድስ ፖሊስ በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠርጣሪ የሆነን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

የ71 አመቱ ግለሰብ በፈረንጆቹ 1994 በሩዋንዳ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጣሪ ናቸው፡፡

የቀድሞው የባንክ ፀሐፊና የመድሃኒት ቤት ባለቤት የሚገደሉ ቱትሲዎችን ዝርዝር አዘጋጅተዋል በሚል ውንጀላ ቀርቦባቸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በቱትሲዎች ላይ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ተሳትፎ አድርገዋልም ነው የተባለው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ሩዋንዳ ግለሰቡ ተላልፈው ይሰጡኝ ብላለች፡፡

100 ቀናት በቆየው የዘር ማጥፋት 800 ሺህ ገደማ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይነገራል፡፡

በቅርቡ ፌሊሴን ካቡጋ የተባለ ነጋዴ የዘር ጭፍጨፋውን በገንዘብ ደግፈሃል በሚል በፓሪስ መያዙ ይታወሳል፡፡

ግለሰቡ ግን ውንጀላውን ውሸት ነው ሲል አስተባብሏል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.