Fana: At a Speed of Life!

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በነዳጅ ምርቶች ግብይት ወቅታዊ ሁኔታ እና የሪፎርም ተግባራት ዙሪያ ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በነዳጅ ምርቶች ግብይት ወቅታዊ ሁኔታ እና የሪፎርም ተግባራት ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡
ውይይቱ የነዳጅ እና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦት ስርጭትና ግብይት ፍትሃዊነት፣ ተደራሽነትና የቁጥጥር ስርዓት ላይ እንዲሁም በዘርፉ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን በመከታተልና በመገምገም የማስተካከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ ታስቦ ነው የተካሄደው፡፡
በውይይቱ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ ቱሳ በነዳጅና ነዳጅ ውጤቶች ግብይት ላይ ለሚታዩ በርካታ ችግሮች መሰረታዊ ምንጮች የነዳጅ ዋጋ ታሪፍና የታሪፍ እዳግ የአሰራር ክፍተቶች ፣ የነዳጅ ግብይት መሠረተ ልማትና ሎጆስትክ ውስንነት ፣ ደካማ የዘርፉ አመራርና አሰራር ፣ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት እና የቤኒዚል አቅርቦት ማነስ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ዳይሬክተሩ በነዳጅና ነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ እየታየ ያለውን ችግር ለመፍታትም የሃገሪቱን የማደያ ብዛትና አቅም በማሳደግ ዘርፉ ለሀገር የኢኮኖሚ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት ያለውን ቁልፍ ድርሻ በሚፈለገው መጠንና አግባብ እዲገነባ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ የክልልና ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች እና የነዳጅ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
በምስክር ስናፍቅ ተጨማሪ መረጃ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.