Fana: At a Speed of Life!

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ለሰራዊቱ 105 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት 105 ሚሊየን ብር የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አድርጓል።
 
በክፍለ ከተማው የሚኖሩ ሴቶችና እናቶች ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት የስንቅ ዝግጅትና የደም ልገሳ መርሃ ግብር አከናውነዋል።
 
ክፍለ ከተማው ከአርሶ አደሮችና የአርሶ አደር ልጆች የተሰበሰቡ 200 ሠንጋዎችንም ለመከላከያ ሰራዊት አበርክቷል።
 
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ነጻነት ዳባ÷ጠላት ሀገር ለማፍረስ የጀመረውን ጦርነት በድል እንወጣዋለን ብለዋል።
 
የአዲስ አበባ ብልጽግና ፖርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መለስ አለም በበኩላቸው÷አሸባሪው ህውሓት ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር አብሮ ኢትዮጵያን ለመውጋት ቢመጣም በአንድነት ቆመን የአባቶቻችንን ታሪክ ለመድገም ዝግጁ ነን ብለዋል።
 
በመርሃ ግብሩ የመከላከያ ሚኒስቴር ተወካዮችም ተገኝተዋል፡፡
 
በትዕግስት አብርሃም
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.