Fana: At a Speed of Life!

የአለም የጤና ድርጅት በአንድ ቀን ብቻ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ቁጥር መመዝገቡን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአለም የጤና ድርጅት በአንድ ቀን ብቻ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ቁጥር መመዝገቡን አስታወቀ፡፡

በዚህም ድርጅቱ እንዳስታወቀው በአለም በአንድ ቀን ብቻ 303 ሺህ 930 ሰዎቸ በቫይረሱ ተይዘዋል።

በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥርም ሕንድ፣ አሜሪካ እና ብራዚል ቀዳሚ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በአለም ዙሪያም 5 ሺህ 500 የሚሆኑ ሰዎችም በ24 ሰዓት ውስጥ ለህልፈት ተዳርገዋልም ነው የተባለው።

ከዚህ ቀደም በአንድ ቀን ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር የተመዘገበው ከአንድ ሳምንት በፊት ሲሆን በእለቱም 306 ሺህ 857 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው እንደነበር ድርጅቱ አስታውቋል።

በዚህም እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ትላንት በሕንድ 94 ሺህ 372፣ በአሜሪካ 45 ሺህ 523 እና በብራዚል 43 ሺህ 718 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

በሌላ በኩል በአውሮፓ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ሲሆን፥ ቫይረሱ ዳግም ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩ እየተነገረ ነው።

ለዚህም በከፍተኛ ሁኔታ ቫይረሱ ጉዳት ባደረሰባቸው አካባቢዎች የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ታውቋል፡፡

ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እንዲያደርጉና አካላዊ ርቀት እንዲጠብቁም ማሳሰቢያ እየተሰጠ ይገኛል።

ቫይረሱ ዳግመኛ ካገረሸባቸው አገሮች መካከል ፔሩ፣ እስራኤል፣ ደቡብ ኮርያ እና አውስትራሊያ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.