Fana: At a Speed of Life!

የአማራና የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአዳማ እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራና የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

የምክክር መድረኩ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና የምክክር ባህልን ማጎልበት ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ውይይቱ ዛሬ መካሄድ የጀመረ ሲሆን እስከ ነገ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በመድረኩ የፖለቲካ አመራሮችና የፓርቲ ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ላይ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ፣ የህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት፣ የሀገር ግንባታ ድርሻ፣ ሰላማዊ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ባህል ግንባታ ላይም ይመከራል፡፡

ኢትዮጵያ ባሳለፈቻቸው የነገስታት፣ የደርግ፣ ኢህአዴግ፣ የለውጥ ጉዞና የወደፊት የፖለቲካ አቅጣጫ ላይም ይመከራል ተብሏል፡፡

በመድረኩ የሀይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሲቪል ማህበራትና ምሁራን ታድመዋል፡፡

በረጋሳ ፍሮምሳ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.